በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በሀዋሳ ክለብ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሰልጠና ተሰጥቷል ፡፡
ቀን ፡- መጋቢት 17/2013 ዓ.ም
ሴንትራል ሆቴል ሀዋሳ
በስልጠናው ላይም 40 የሚሆኑ አትሌቶች የቅርጫት ኳስ ተጫዋቾች ፣ የእግር ኳስ ተወካዮችና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
ስልጠናው የተሰጠው በትምህርትና ስልጠና ዳሬክቶሬት ባለሙያዎች ሲሆን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መስረታዊ ጉዳዮች፤ በየደረጃው ባሉ የአሰራር ስርዓቶች እና አደረጃጀቶች ፤ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ በተከለከሉ የስፖርት አበረታች ቅመሞችና ዘዴዎች ዙሪያ ያተረ ነው።
እንደዚህ አይነት ተመሳሳይ ስልጠናዎች በቀጣይም ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን ታድጊ አትሌቶች እራሳቸውን ከዶፒንግ በመጠበቅ ከሚደርሱባቸው ተያያዥ ችግሮች መጠበቅ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *