በስትራቴጂክ ዕቅድና የስራ አመራር ላይ ስለጠና ተሰጠ፡፡
በስትራቴጂክ ዕቅድና የሥራ አመራር ላይ ያተኮር የሁለት ቀን ሥልጠና ለኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን መካከለኛ፣ የበታች አመራር አካላትና ሠራተኞች ተሰጠ፡፡
ከሚያዚያ 4 እስከ 5 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ኢፍታህ ሆቴል የተካሄደው የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ የመከከለኛ አመራርና ሰራተኛው አካላቱ ስልታዊ በሆነ የዕቅድ አወጣጠና የሥራ አመራር ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ እደሆን በዚህ ወቅት ተገልፃል፡፡
ስልጠናው የተቋሙን ዕቅድ አወጣጥና የሥራ አመራር ሰልት የበለጠ አሳታፊ ተግባራዊ እንዲሁም የተጠያቂነትና የባለቤትነት መንፈስ የተላበሰ እዲሆን የሚደረገውን ጥረት እዲሚያጎለብት ተመልክቷል ፡፡
በስልጠናው ወቅት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ተገኝተው እደገለፁት የውጤት ተኮር ሥራዓት ዕቀድ ዝግጅትና የትግበራ ደረጃወዎችን በሚገባ በማወቅ በዕምነት ሊተገበር እደሚገባ በማሳሰብ አመራር አካላቱና ሰራተኛው ያገኘውን ዕውቀት የራሱ አድርጎ የተቋሙን ስራቴጂክ ግብ በማሳካት ውጤት ያስመዘግባል የሚል እምነት እዳላቸው ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው ከኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሺን በመጡ ባለሞያዎች የተሰጠ ሲሆን የውጤት ተኮር ሥራ አመራር (የወ.ተ.ሰ) ማዕቅፍ እና የትግበራ ደረጃዎች በሚሉ ዋና ዋና ርዕሶች በስልጠናው ትኩረት የተደረገበት ነው፡፡
የስልጠናው ተሳታፊ ሠራተኞች መድረኩን አሰመልክቶ የተሰጠው ስልጠና የተሻለ ግንዛቤ እደፈጠረላቸው፤ ለቀጣይ ሥራአችን በተሻለ ጥራት ለመተግበር እድንችል መንገዱን ያሳየን መድረክ ነው ብለዋል፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር የተሠጠ ሲሆን የመጀመሪው ዙር ሰልጣኞች ከሚያዚያ 04 እስከ 05 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ተሰጥቷል ፡፡

By Ermias