የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባባር በደቡብ ክልል ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተመረጡ ለስፖርት መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ
በተመሳሳይ ለዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች በኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በደቡብ ክልል ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተመረጡ በአትሌቲክስ ፣ በመረብ ኳስ፣ በቅርጫት ኳስና በእጅ ኳስ በመጀመሪያ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና በመከታተል ላይ ለሚገኙ የስፖርት መምህራን በኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተካሄደ፡፡
መድረኩን ላይ የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ተገኝተው መልዕክት በመስተላለፍ በይፋ ከፈተውታል፡፡
ታህሣሥ 05 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባባር በመጀመሪያ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ለሚከታተሉ የስፖርት መምህራን ፤ታህሣሥ 06 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ለዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች በሆሳህና ከዋና መ/ቤት በሄዱ ባለሙያዎች በስፖርት በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትለው ጉዳት፣ በወንጀል ህጉ እና በየደረጃው በተዘረጉ የአሠራር ሥርአቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ከመሰጠቱም በላይ ከተሳታፊዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል ፡፡
በሆሳህና በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ 120 የስፖርት መምህራን እና 30 የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች የተሳተፉ መሆናቸው ታውቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *