በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አትሌቲክስ ክለብ ለስፖርት ባለሞያዎችና አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመለከቱ ጉዳዮች በዩኒቭርሲቲው አትሌቲክሰ የስልጠና ካሪኩለም ውስጥ ተካተው ተግባራዊ በሚደረጉበት ሁኔታ ላይም ውይይት ተደርጓል።
ለሦስት ቀን ሲሰጥ የነበረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተጠናቋል
ጥቅምት 05/2014 ዓ.ም
ETH-NADA has provided awareness creation trainings for athlete support personnel and Athletes of Debre Birhan University Athletics Club.
More than 65 Athletes supporter personal and athletes from University Athletics Club and those who did not previously get the training attended the training session.
በየደረጃው የሚገኙ ስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች በጉዳዩ ዙሪያ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማስቻል የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ቀደም ሲል ጀምሮ የተለያዩ የህዝብ ንቅናቄ ስልጠናዎችንና የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረኮችን ሲያካሂድ የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአትሌቲክስ ክለብ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-NADA/ ጋር በመተባበር የስፖርት ባለሞያዎችና አትሌቶች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች፤ በምርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ በአትሌቶች መብቶችና ግዴታዎች እዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በዩኒቭርሲቲው የስብስባ አደራሽ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ይህም ስልጠና በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን በሌሎች የትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላት ለሚገኙ ባለሞያዎችና አትሌቶች ተደራሽ ለማድረግ እና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ባለስልጣን መሥራቤቱ ትኩረት ሰጦ የሚሰራ ይሆናል፡፡
በዚህሥልጠና ላይ ከ65 የሚበልጡ የድብረ ብርሃን የኒቭርሲቲ የአትሌቲክስ ክለብ የስፖርት ባለሞያዎችና አትሌቶች እንዲሁም ከዚህ ቀደምሥልጠናውን ያልወሰዱ የዩኒቭረሲቲው የስፖርት ባለሞያዎችና አትሌቶች ተሳትፈዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *