ባለሞያዎች በተለያዩ አለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የፀረ-አበረታች ቅመሞች (Anti-Doping) ተቋማት ውስጥ ያላቸው ተሳትፎና እና ውክልና ከፍ እንዲል ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራት ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) ከተቋቋመ ገና አጭር ጊዜ ያስቆጠረ ቢሆንም ባለፉት ጊዜያት ተቋማዊ አቅሙን በማጎልበት እና የአሰራር ስርዓቶችን በአግባቡ በመዘርጋት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተሸጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት በነበረው ውስን ጊዜ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ምርመራና ቁጥጥርን ጨምሮ ዘርፈ-ብዙ ተግባራትን ማከናወን የተቻለ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ጭምር ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

ፅ/ቤቱ በአገር ውስጥ ከሚያካሂደው የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የመከላከልና የመቆጣጠር ተግባር በተጨማሪ በአለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት በመሳተፍ የበኩላችንን ገንቢ ሚና ለመጫወትና አለም አቀፍ ግንኙነቱንም ለማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በተቋማችን በተለያዩ ደረጃዎች እያገለገሉ ያሉ ሙያተኞች በአለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ውክልና እንዲያገኙ ለማድረግ ሰፊ ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩ ሲሆን አቶ ይርሳው ዘውዴ የአፍሪካ የዳኝነት ፓናል (Africa Continental Result Management Panel) አባል ሆነው መግባት ችለዋል፡፡ ይህ ፓናልም በአፍሪካ ደረጃ የሚፈፀሙ የአበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰቶችን በመመልከት ዳኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ ዶ/ር ድረስባቸው ኃይሌም በአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) ውስጥ የቴክኒካል ኮሚቴ አባል በመሆን ቀደም ሲል ጀምሮ በብቃት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይም አለም አቀፍ ተሳትፎውን የማጎልበት ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *