ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለተጠሪ ተቋማት ልምድ ማጋራት የሚችልበት የተሻለ ቁመና ላይ እንደሆነ ተጠቆመ።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የድጋፍ ፣ ክትትል እና ግምገማ ኮሚቴ ባደረገው ምልከታ የኢትዮጵያ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ለተጠሪ ተቋማት ልምድ ማጋራት የሚችልበት የተሻለ ቁመና ላይ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014
ኮሚቴው በኢትዮጵያ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን መስሪያ ቤት በመገኘት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም እና አጠቃላይ እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች በዋና ዳይሬክተር በአቶ መኮንን ይደርሳል እና በየክፍሉ ዳይሬክቶሬቶች አማካኝነት በሰነድ የተደገፈ ገለፃል ለኮሚቴ አባላቱ ተደርጓል፡፡
የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል የተቋሙን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ፥ ከባለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸማችንን በደንብ በመገምገም በያዝነው በጀት ዓመት በተጠናከረ መልኩ ወደስራ መግባት መቻሉን ጠቁመው ተቋማችን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገመገም ከመሆኑም አንጻር ሁሌም በችግሮች መሀል ሆነንም ስራዎቻችን በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
የኮሚቴው አባላት በበኩላቸው ተቋሙ አለም አቀፍ ህግና ደንቦችን መሰረት አድርጎ የሚሰራ ከመሆኑ አንጻር ያሉትን መልካም ጅምሮች በማጠናክር ለሌሎቸ ተጠሪ ተቋማተ ልምዱን ማጋራት የሚችልበት የተሻለ ቁመና ላይ እንዳለ ተናግረዋል ። አያይዘውም ያሉበትን አገር አቀፍም ሆነ አለም አቀፍ ተግዳሮቶቸን ተቋቁሞ ስራዎችን ማከናወን ላይ ተጠናክሮም ሊቀጥል እንደሚገባም ጠቁመዋል።

By Ermias