ታዳጊ ወጣቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጎልበት የOutreaching ፕሮግራም በአሰላ ከተማ አረንጓዴ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ቀን፡-የካቲት 26/2013
አሰላ አረንጓዴ ስታዲየም
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) በአሰላ ከተማ በሚካሄደው 2ኛው የኢትዮጲያ ከ15፣ 16፣ 17 ዓመት እና 18 ዓመት በታች የታዳጊዎች የአትሌቲክስ ሻምፕዮና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ተተኪ ስፖርተኞች፣ የስፖርት ባለሞያዎች፣ የስፖርት አመራሮች፣ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎችንና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የትምህርት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ አላማ ታዳጊ ስፖርተኞች ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዲሁም ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይንም ዶፒንግ ነፃ የሆነ ስፖርት እንዲስፋፋ እና በትክክለኛው መንገድ ተወዳድረው ውጤታማ የሆኑ ጤናማ ስፖርተኞች እንዲፈሩ ለማስቻል የታሰበ ፕሮግራም ነው፡፡
በፕሮግራሙ ላይ በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የህትመት ውጤቶች ፤ በአማርኛ ቋንቋ እና በኦሮምኛ የተዘጋጁ ብሮሽሮች የተስራጩ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በየውድድር ስፍራዎች ተሰቅለዋል፡፡ በተጨማሪም በጥያቄ እና መልስ (Play True Quiz Computer Game) እና አዝናኝ በሆኑ ጨዋታዎች አማካይነት በዶፒንግ ዙሪያ ግናዛቤ ለመፍጥተ ተቸሏል፡፡ ውድድሩም ከየካቲት23-28 /2013 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል፡፡
May be an image of one or more people, people standing and outdoors
May be an image of one or more people and people standing
May be an image of 1 person, standing and outdoors
May be an image of 1 person and standing

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *