“ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርተኞች እናፈራለን” # ከኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ
(ግንቦት 13/2013 ) የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ (ቡናማዎቹ ) ቡድን አባላት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
(ሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ለኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች እና የህክምና ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም በዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት የተሰጠ ሲሆን ከ30 የሚበልጡ የቡድኑ አባላት ስልጠናዉን ተከታትለውታል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ ተጫዋቾች እና የቡድኑ አባላት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማጎልበት፤ እራሳቸውን ከዶፒንግ እንዲጠብቁ ለማስቻል ነው፡፡
ስልጠናው በዶፒንግ ምንነት፣ ህግ ጥሰት፣የአትሌቶች መብትና ግዴታ፣የዶፒንግ የምርመራ ሂደት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ነው ስልጠናው የተሰጠው፡፡
ኢትዮጲያ ቡና በ2013 የቤትኪንግ ኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ በ37 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ አንጋፋ ክለብ ነው ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *