በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ለሚገኘው ዘቢዳር አትሌቲክስ ክለብ አትሌቶችና ለድጋፍ ሰጨ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጯ ስልጠና ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን/ ETH ADA/ 40 ለሚሆኑ አትሌቶችና ለድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሚዯዚያ 04 ቀን 2014 ዓ.ም ተሰጠ፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን/ETH ADA/ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ በመድረኩ ላይ የተገኙት ባስተላለፉት መልዕክት ዶፒንግ የስፖርቱን ፍታሐዊ የውድድር ሥርአት ላይ ተፅኖ ከመፍጠሩም በላይ የህበረተሰቡ የጤና ችግር ነው፡፡ በመሆኑም ስፖርተኞችም ሆነ ባለሞያው ግንዛቤ ጨብጦ እራሱን ከችግሩ ማራቅ እደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም በአሁን ግዜ ዶፒንግን ተጠቅሜ በማጭበርበር ማሸነፍ አይቻልም፣ በተለይ የተጨበረበረ ማስረጃ በማቅረብ እራስን ንፁህ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ተቀባይንት የሌለው የወንጀል ተግባር ነው፡፡ ሁሉም እረሱን ከድርጊቱ ማራቅ እዳለበት አሳስበዋል፡፡
ስልጠናዉን በገላፃ ያቀረቡት የትምህርት፣ስልጠናና ጥናትና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ከፈተኛ የስልጠና ባለሞያ የሆኑት አቶ ሐብታሙ ካሱ ናቸዉ፡፡

By Ermias