የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የሆነው አሌክስ ተሰማ ሐይሌ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ፈፅሞ በመገኘቱ የማስጠንቀቂያ ቅጣት ተላልፎበታል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በእግር ኳስ ስፖርት ላይ የሚያካሂደውን ምርመራና ቁጥጥር በማጠናከር ላይ የሚገኝ ሲሆን በሐዋሳ ከተማ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ውድድር ላይ እ.ኤ.አ ታህሳስ 10/2021 በተደረገው የአበረታች ቅመሞች ምርመራ የእግር ኳስ ተጫዋች አሌክስ የተከለከለ አበረታች ቅመም መጠቀሙን የሚያመላክት ውጤት ማግኘት ተችሏል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለስልጣኑ እ.ኤ.አ ከመጋቢት 23/2022 ጀምሮ ተጫዋቹ በየትኛውም የስፖርት ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ጊዜያዊ እገዳ በመጣል በጉዳዩ ዙሪያ ጥልቀት ያለው ተጨማሪ ምርመራ እና የማጣራት ተግባራትን ሲያከናው የቆየ ሲሆን Cathinone የተባለውን የተከለከለ አበረታች ቅመም የተጠቀመ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የዳኝነት ኮሚቴ (Hearing Panel) የላቦራቶሪ ውጤትን ጨምሮ የቀረበለትን መረጃና ማስረጃ መርምሮ በጉዳዩ ላይ ነፃና ገለልተኛ በሆነ መልኩ ባስቻለው ችሎት ተጫዋቹ ያለው ግንዛቤ ዝቅተኛ መሆኑን እንዲሁም የተከለከለውን አበረታች ቅመም ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት ያልተጠቀመ መሆኑን በምክንያትነት በማስቀመጥ ተጫዋች አሌክስ ለፈፀመው የህግ ጥሰት የማስጠንቀቂያ ቅጣት እንዲተላለፍበት ውሳኔ አስተላልፏል።
በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ኮሚቴ (Hearing Panel) በተላለፈው የቅጣት ውሳኔ ላይ በባለስልጣኑ ወይም ጉዳዩ በሚመለከተው ሌላ አካል ይግባኝ (Appeal) ሊቀርብበት እንደሚችልም ተመላክቷል።
May be an image of 1 person and standing
በየደረጃው አበረታች በሆነ መልኩ የተጀመረው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ትግል ወይም ንፁህ ስፖርት የማስፋፋት እንቅስቃሴ በየደረጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።

By Ermias