የምስራቅ አፍሪካ አገሮችና የአፍሪካ ዞን 5 የፀረ-ዶፒንግ ድርጅት አባል አገራት መደበኛ የፀረ-ዶፒንግ ስብሰባ በአገራችን አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል፡፡

ቀን፡ ሰኔ 03/2011 ዓ.ም

አገራችን ኢትዮጵያ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት በየደረጃው ዘርፈ-ብዙ ጥረቶችን እያደረገች መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ ዓመት የሚካሄደውን የምስራቅ አፍሪካ አገሮችና የአፍሪካ ዞን 5 የፀረ-ዶፒንግ ድርጅት አባል አገራት መደበኛ የፀረ-ዶፒንግ ስብሰባ ታስተናግዳለች፡፡

ስብሰባው በአዲስ አበባ ከተማ ራዲሰን ብሉ ሆቴል ከሰኔ 5-6/2011 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን በቀጠናው የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን መከላከልና መቆጣጠር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በጥልቀት ይመክራል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ስራውን እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎችንና የአሰራር ስርዓቶችን በጠበቀ መልኩ በመንቀሳቀስ ረገድ የአገራችን ተሞክሮዎች ተቀምረው ለሌሎች አገሮች የሚቀርቡ ይሆናል፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ አገራትም ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *