የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
ቀን፤ ሰኞ ጥር 08/2015 ዓ.ም አዳማ ከተማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ በ2015 የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ የባለስልጣኑ ዳይሬክቶሬቶች እና ቡድን መሪዎች ባሉበት ውይይትና ግምገማ እያካሄደ ነው ፡፡
በዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ተገኝተው ፕሮግራሙን የከፈቱት ሲሆን በአዲሱ የሰራተኞች የስራ ስምሪት ድልድል ላይ እና የገልጋይነት አመራርነት (servant leadership) በሚመለከት ለተቋሙ የስራ ከፍል ኃላፊዎች ገለጻ እየሰጡ ይገኛል።
የገልጋይነት አመራርነት (servant leadership) መርሆችን የተላበሰ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መፋጠር እንደ ተቋም የምንከተለው ስርዓት ነው ብለዋል በገለጻቸው ፡፡
መድረኩ አንድ ቀን የሚቆይ ይሆናል

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *