የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች የ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጻምና የ2014 እቅዳቸዉን በአዳማ ከተማ እየገመገሙ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ሠራተኞች፣ በ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ በአዳማ ሄልዝ ሆቴል የስብሰባ አዳራሽ ውይይት አካሄዱ፡፡ በነሓሴ 08 ቀን 2013 ዓ.ም የተካሄደውን ውይይት፣ የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር፣ ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል በንግግር ከፍተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ውይይቱ በበጀት ዓመቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን መሠረት በማድረግ፣ያጋጠሙ ችግሮችንና ክፍተቶችን ለይቶ በማውጣት ለቀጣይ ክንውኖቻችን ትምህርት የምንወስድበትና እቅዶቻችንን አስተካክለን ለመጓዝ የሚጠቅመን መሆኑን በመረዳት፣ ሁሉም የጽ/ቤቱ ሠራተኞች የሚቀርበውን የአፈፃፀም ሪፖርት መነሻ በማድረግ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማሳሰብ የውይይት መድረኩን ከፍተዋል፡፡
የጽ/ቤቱ የእቅድ፣በጀት፤ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣አቶ ፍቅሩ ንጉሴ፣ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸው ሥራዎች በሚዛናዊ ስኮር ካርድ መሰረት መለካቱን በመጥቀስ፣ የተከናወኑ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በአቶ ፍክሩ ንጉሴ እንደተብራራው፣ በጽ/ቤቱ የዋና አገልግሎቶች አፈፃፀም መሰረት፣በትምህርት እና ሥልጠና እና በምርመራና ቁጥጥር ስራዎች ክፍተኛ ውጤት መመዝገቡን፤ የደንበኞች የአገልግሎት እርካታ መለካት፤ በዕቅድ ከተያዙት ተግባራት አንፃር ሲገመገም፣ ደግሞ ከተከናወኑ ተግባራት አንፃር በበጀት ዓመቱ ዝቅተኛ ውጤት መመዝገቡን መረዳት ይቻላል፡፡
የጽ/ቤቱ የዕቅድ አፈፃፀም መረጃ መሠረት በማድረግ በተካሄደው ውይይት፣”ለአፈፃፀሙ ዝቅ ማለት ምክንያቱ ምንድን ነው? ለዚህ ውጤት መመዝገብስ የነበሩ ተግዳሮቶች ምን ነበሩ?” የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በሠራተኞች የተነሱ ሲሆን፣ ለጥያቄዎቹም የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር በአቶ መኮንን ይደርሳል እና በም/ዋና ዳይሬክተሯ በወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ጽ/ቤቱ፣ በበጀት ዓመቱ ካከናወናቸው ሥራዎች ውስጥ በጠንካራ ጎኑ የሚነሱ በርካታ ነገሮች መኖራቸውን የተገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥ፤ቀደም ሲል ከነበረው በተለየ መልኩ በ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ ለመሳተፍ ፤የምርመራና ቁጥጥር፤የትምርህት፣ስልጠናና የህዝብ ንቅናቄ፤ የሽንንትና የABP ምርመራዎችን፤ትኩረት ተሠጥቶ የተከናወኑ ሥራዎች መሆናቸዉን፤ ከውድድር ጊዜ ውጭ ሰፊ ምርመራና ቁጥጥር መካሄዷቸውን፤የተቋሙን ውጤታማነት ለማጎልበት፣ አደረጃጀቱን በአዲስ መልክ የመከለስና የማጠናከር ወዘተ..ስራ መስራታቸዉ፤ተገልፃል፡፡
በውይይቱ መጨረሻ፣ ዋና ዳይሬክተሩ፣ አቶ መኮነን ይደርሳል፣ በተሳታፊዎች የተዘረዘሩት አስተያየቶች፣ ለጽ/ቤቱ ቀጣይ ሥራ አቅም የሚሆኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ በበጀት ዓመት ፅ/ቤቱ ያስመዘገበው ውጤት አጥጋቢ ቢሆንም፣ የ2014 በጀት ዓመት እቅዳችንን በ2013 በጀት ዓመት የጎደሉንን መሙላት በሚያስችለን መልኩ ለመፈፀም በቁጭት ከተነሳሳንና ጠንክረን ከሠራን የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደማያዳግተን ሁላችንም መገንዘብና የግልም ሆነ የጋራ ርብርብ ለማድረግ መነሳት ይኖርብናል በማለት አሳስበዋል፤ የእለቱ ውይይትም በዚሁ ተጠናቋል፡፡
ውይይቱ በነገው ቀንም ቀጥሎ ይውላል፡፡ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *