በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ሲካሄድ የነበረው የግንዛቤ ማሰጨበጫ እና ንቅናቄ ፕሮግም ለድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በመስጠት ተጠናቋል ፡፡

(ግንቦት 13 /2013 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ “ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርተኞች እናፈራለን” በሚል መሪ ቃል በቤትኪንግ ኢትዮጲያ ፕሪምየር ሊግ ላይ እየተሳተፉ ለሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ በዚህ ሳምንት በሐዋሳ ከተማ ሲያካሂድ ቆይቷል ፡፡

በዚህም የግንዛቤ ማስስጨበጫ እና የንቅናቄ ፕሮግራም ላይ በአብዛኛው የክለባቱ ተጫዋቾች አሰልጣኞችና የህክምና ባለሙያዎችን ተደራሽ ማድረግ የቻለ ሲሆን በእግር ኳሱ ላይ ዶፒንግ የሚያስከትለውን ችግር ለመቀነስና ለመቆጣጠር አይነተኛ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል ፡፡

በመሆኑም እንደነዚህ አይነት ስልጠናዎችን በቀጣይ በስፋት ለመስጠትና አስፈላጊውን ድጋፍ ጽ/ቤቱ ለየክለቦቹ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ተነግሯል ፡፡

ስልጠናው ያለንንን ግንዛቤ ከማስፋትም ባሻገር እራሳችንን ከዶፒንግ በመጠበቅ ሊከሰቱ በሚችሉ የጤና እና ተያያዥ ማህበራዊ ችግሮች እንዴት መጠንቀቅ እንዳለብን ግንዛቤ ፈጥሮልናል ሲሉ የየክለቦቹ ተጫዋቾችና ባለሙያዎች በስልጠናው ወቅት ተናግረዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *