ማሰልጠኛ ተቋማችን የዶፒንግ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ፡- አቶ ታደሰ በኪ የጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል የትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር
ቀን፡-የካቲት 27/2014 ዓ.ም
ቦታ፡- (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል)
አሰላ ከተማ (ETH-ADA እሁድ የካቲት 28/2014 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከ150 በላይ ለሚሆኑ ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል አትሌቶች ፤ ቡድን አመራሮች እና አሰልጣኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማሰልጠኛ ማዕከሉ ትምህርት እና ስልጠና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ በኪ እንዳሉት ስፖርተኞቻችን ከዶፒንግን እራሳቸውን በመጠበቅ በሀገርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው እንዲገኙ የሚያስችላቸውን የተለያዩ ስራዎችን እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል፡፡
ማሰልጠኛ ተቋሙ የዶፒንግን ጉዳይ በስልጠና ማኗሎች በማካተት አጫጭር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት እና በአሰልጠኞች አማካኝነት አትሌቶች እራሳቸውን ከዶፒንግ መጠብቅ የሚችሉበትን አቅም እየፈጠረ እንደሆነም ጠቁመዋል ፡፡
በድጋፍና ክትትል ወቅትም የአሰልጣኞች አመታዊ ዕቅድ ላይ የዶፒንግ ጽንሰ ሀሳብ በማካተት በተቋሙ በመስራት ላይ መሆኑን ማየት ተችሏል ፡፡

By Ermias