የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) በአሰላ ከተማ በሚካሄደው 11ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ የተተኪ ስፖርተኞች ፣የክለብ ስፖርተኞች፣የስፖርት ባለሞያዎች እና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የትምህርት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ ከጥር 23-28/ 2015 ዓ/ም ድረስ ሲቆይ ታዳጊ ስፖርተኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ጤናማ ስፖርተኞች እንዲፈሩ ለማስቻል አላማ ያደረገ ፕሮግራም ነው፡፡
በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ብሮሽሮች ፣ ቲሸርቶች የተስራጩ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በየውድድር ስፍራዎች ተሰቅለዋል ፡፡
በተጨማሪም በጥያቄ እና መልስ (Play True Quiz Computer Game) እና አዝናኝ በሆኑ ጨዋታዎች አማካይነት በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *