ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና ከሲዳማ ክልል ለተወጣጡ
Read Time:39 Second
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል እና ከሲዳማ ክልል ለተወጣጡ ለህክምና ፤ የስነ-ምግብ እና ወጌሻ ባለሞያዎች በተዘጋጀ መድርክ ላይ ‹‹የስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplements) ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጋር ያላቸው ግኑኝነትና በተያያዥ ርዕሶች›› ላይ በበይነ መረብ (zoom meeting) አማካኝነት ስልጠና ተሰጠ፡፡
መጋቢት፡- 14/2013 ዓ.ም /
ሐዋሳ፡- ሴንትራል ሆቴል
ስልጠናውን የሰጡት ወ/ሮ ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ የህክምና ባለሞያ ናቸው፡፡
የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ምንነት፤ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ስላላቸው ግኑኝነት፤ በተከለከሉ መድሀኒቶች ዝርዝር ፤ በህመም ምክንያት የሚፈቀዱ የተከለከሉ ቅመሞች ፤ የህክምና ስርዓቶችና መፍቀጃ ቅጽ ዙሪያ እንዲሁም እንዴት እንጠንቀቅ ? እንዴትስ እናስጠንቅቅ? የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ትኩረት የተደረገባቸው ናቸው ፡፡
በተጨማሪም ባለሙያዎቹ በቡድን የተወያዩበትን ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆን በተለያዩ ጉዳዮች ከባለሙያዎቹ ለተነሱት ጥያቄዎች በምክትል ዳሬክተሯ በወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡





Related Post
በሀዋሳ ክለብ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሰልጠና ተሰጥቷል ፡፡
በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በሀዋሳ ክለብ ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ ስፖርተኞች፣ አሰልጣኞች እና አመራሮች ሰልጠና ተሰጥቷል ፡፡ ቀን ፡-...
# ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርት እና ስፖርተኞችን እናፈራለን !!!
# ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርት እና ስፖርተኞችን እናፈራለን !!! በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው ለስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ስፖርተኞች አሰልጣኞች እና የስፖርት...
ሀገረሰላማ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል
በአዲሲቷ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ውስጥ በሚገኘው ሀገረሰላማ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ አትሌቶች እና አሰልጣኞች በዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና...
ለሐዋሳ ዩንቨርስቲ የ2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ድግሪ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች
ለሐዋሳ ዩንቨርስቲ የ2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ድግሪ የስፖርት ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች እና መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና...
አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግን) በመከላከል ረገድ የህክምና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡
አበረታች ቅመሞችን (ዶፒንግን) በመከላከል ረገድ የህክምና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ፡፡ ቀን፡- መጋቢት 13/ 2013 ዓ.ም ሐዋሳ ሴንትራል ሆቴል በሐዋሳ...
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳብ ስልጠና ተሰጠ::
ቀን፡- ሀሙስ መጋቢት 9/2013 ዓ.ም ቦታ ፡- ጥሩነሽ ዲባባ ሆቴል ለገጣፎ እና አሰለፈች ሆቴል አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች...
Average Rating