ለሃገረ-ሰላም እና ለቦቆጂ ማሰልጠኛ ማዕከላት ትምህርታዊ ስልጠና ተሰጠ።
አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ዙሪያ ለበቆጂ እና ለሃገረ ሰላም ማሰልጠኛ ማዕከላት ታዳጊ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ባለሞያዎች በባህር ዳር የግንዛቤ ማጎልበቻ ትምህርት ተሰጥቷል።
ትምህርቱን የሰጡት የትምህርት፣ሥልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ናቸው።
መርሃግብሩ ስለዶፒንግ ምንነት ከማብራራት ጋር በተጓዳኝ የሚያስከትለው ጉዳት፣የወንጀል ህጉን አንዲሁም አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን ለመቆጣጠር በተዘረጋ የአሠራር ስርአቶችና በተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃና የቡድን ውይይት የቀረበበት ነው።