የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ላይ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
ቀን፤ ሐሙስ ጥር 26/2014 ዓ.ም አዳማ ከተማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ በ2014 የመጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት ባከናወኗቸው ተግባራት ላይ የባለስልጣኑ ዳይሬክቶሬቶችና ሰራተኞች ባሉበት ውይይትና ግምገማ እያካሄደ ነው ፡፡
በዚህ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ተገኝተው በንግግር ከፍተውታል ፡፡ እንደነዚህ አይነት የግምገማ መድረኮች ለተቋሙ ከፍተኛ ሚና እናዳለው ጠቁመው ሰራተኞች የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በጠዋቱ ፕሮግራም የተቋሙ መጀመሪያው ግማሽ በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት በወ/ሮ ስርጉት በየነ የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳ/ዳይሬክተር ቀርቧል፡፡
ውይይቱ ከምሳ በኃላ የሚቀጥል ሲሆን የ6 ወር ሥራ አፈጻጸም ላይ በተነሱ ጥያቄዎችና አስተያያቶች ውይይት የሚደረግ ይሆናል፡፡
Previous post በ2ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮ እና በ38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ላይ የፀረ -ዶፒንግ Outreaching ኘሮግራም በባህር ዳር ተካሄደ።
Next post የ6 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በማካሄድ የቀጣይ የ6 ወር የዕቅድ ዝግጅት ኦረንቴሽን ተሰጠ::