የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) ለ51ኛ ግዜ ከመጋቢት19 ቀን እስከ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም ድረስ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም በተካሄድው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም አካሄዷል፡፡
ይህ የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም አትሌቶች፣የአትሌቶች ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች እየተዝናኑና በቀላሉ በስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን ፅንሰ ሃሳብንና ዶፒንግን በመከላከልና ለመቆጣጠር የተዘረጉ የአሰራር ስርአቶችን በቀላሉ እዲረዷቸውና ግንዛቤያቸውን በማዳበር ለንፁ ስፖርት መስፋፋት የበኩላቸውን ሚና እዲወጡ የሚያስችል ነው፡፡
በፕሮግራሙ በስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ትምህርታዊ መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ በተጨማሪም በተሳታፊዎች መካከል የጥያቄና መልስ፤ የናሙና መሰብሰቢያ ኪቶች አይነታቸውንና አጠቃቀማቸው(Samples of urine Testing kits)ላይ ገለፃእዲሁም ሌሎችዓይት ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡ ለተሳታፊዎች የተለያዩ ቲ-ሸርቶች፣እስክሪበቶዎች፣ኩፊያዎች በሽልማት መልክ ተበርክቶላቸዋል፡፡
በስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን ፅንሰ ሃሳብንና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መረጃ የሚሰጡ የተዘጋጁ ብሮሸሮች ተሰራጭተዋል፡፡