ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አመራሮችና ለስፖርት ባለሞያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤና ውይይት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
ሚያዚያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም
ቦንጋ ከተማ
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ ባስልጣን መስሪያ ቤቱ በበስፖርቱ ዘርፍ ስጋት እየሆነ የመጣውን ዶፒንግን የመጠቀም አዝማሚያ ከምንጩ ለማድረቅ ጤናማ ስፖርተኞችን ለማፍራት እንዲያስችል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ምክትል ዋና ዳይሬክሯ ይህን የተናገሩት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤና ውይይት ፕሮግራም በታካሄደበት ወቅት ነው፡፡
በአገራችንን ንፀህ ስፖርት ለማስፋፋትና ጤናማ ስፖርተኞችን ለማፍራት፣ የዶፒንግ ህግ ጥሰት እዳይስፋፋ ቅድሚያ የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጥ እንደሚገባ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ከዚህ አልፎ በዶፒንግ የህግ ጥሰት የሚፈፅሙ ካላትን ደግሞ በህጉ ተጠያቂ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡
የፀረ-ዶፒንግ ጉዳይ የሚከታተል ባለሙያ በክልሉ መዋቅር በሚካተትበት ሁኔታ ላይ እዲሁም ስለሰፖርት አበረታች ቅመሞች ጉዳይ በስልጠና ካሪኩለም ውስጥ ተካቶ በሚተገበርበት ዙሪያም ከክልሉ ቢሮ ጋር ውይይት ተደርገዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ለመከላክልና ለመቆጣተር እተደረገ ስላለው ጥረት፤ በዶፒንግ ምንነት፣በተዘረጉ አሰራር ስርአቶች፣በተቋሙ አደረጃጀት፣በህግ ማዕቅፎችና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ገለፃ ተደርጓል፡;
የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታውን አባይነ በውይይቱ ላይ እደገለፁት ክልሉ አዲስ ከመሆኑ አንፃር ተቋም እየገነባን ነው፤ አጋጣሚው ጥሩ ነው፤ የዶፒንግ ጉዳይ በክልሉ መዋቅር ውስጥ አካተን ተግባራዊ ለማድረግ እንሰራለን፤ባለሞያም እንመድባለን፤ ከባለስልጣ መስራቤቱም ጋር ተቀራርበን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህን መድረክ አዘጋጅቶ ግንዛቤ ስላስቸበጣቸው ምስጋና አቅርበው ውይይቱ ተጠቋል፡፡