ለጂማ ዮኒቨርስቲ ስፖርት አካዳሚ መምህራን ና ለስፖርት ሳይንስ ተማሪዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም ተካሄደ ።
የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH ADA /ሚያዝያ 06 ቀን 2014ዓ.ም ለስፖርት ሳይንስ የመጀሪያ እና ለሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች እዲሁም ሚያዝያ 07/2014 ዓ.ም ለአካዳሚው መምህራን በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሠረታዊ ጉዳዬች ፤በተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች፣ በአደረጃቱ፤ በወንጀል ህጉ፣የጤና ጉዳቱና በተያያዥ ጉቸዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሂዷል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስፖርት አካደሚዎች ዶፒንግ በስፖርቱ ልማት ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ የስፖርቱ ማህበረሰብ እንዲያውቀው ከማድረግ አንፃር ድርሻቸው ከፍተኛ እደሆነ የገለፁት የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅሞች ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ የስፖርት አካዳሚ የስፖርት ባለሞያዎችን በስነምግባር ና በውዕውቀት ለማነፅ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባችው የስፖርት ሙሁራን ዶፓንግ የሚያስከትለውን ጉዳት ህብረተሰብ የተረዳ አዲሆን የማስተማር ሀላፊነት አለባችው ብለዋል።