ታህሳስ 17/2011 ዓ.ም

በአገራችን በርካታ ባለሞያዎች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሰልጥነው በአሰልጣኝነት፣ በዳኝነት፣ በኢንስትራክተርነት እና በመሳሰሉት ዘርፎች በማገልገል ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም እነዚህ የስፖርት ባለሞያዎች በአገር አቀፍ ደረጃ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ሰፊ ሚና እንደሚጫወቱ ይታመናል፡፡

በመሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች/የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ እና ከላይ እንደተገለፀው በ19 የስፖርት አይነቶች በአሰልጣኝነት፣ በዳኝነት እና በኢንስትራክተርነት ለሚያገለግሉ 610 የስፖርት ባለሞያዎች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ መሰረታዊ ጉዳዮች፣ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርዓቶችና አደረጃጀቶች፤ በህግ ማዕቀፎች እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በአዳማ ከተማ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ይህ ስልጠና በቀጣይም ተጠንክሮ የሚቀጥል ሲሆን በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላትን ተደራሽ ለማድረግ እና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ለመፍጠር ፅ/ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *