በኢትዮጵያ ብዊሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (Ethiopia National Anti-Doping Office) ቋሚ ሎጎ ዙሪያ አስተያየት እንድተሰጡን ስልመጋበዝ

ቀደም ባሉት ዓመታት የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የአገራችን ስፖርት በተለይም የአትሌቲክሱ ስጋት ወደመሆን ተሸጋግሮ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይህን ችግር በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የኢትዮያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት በሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 400/2009 ተቋቁሞ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ የተሸጋገረ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ፅ/ቤቱ በአገራችን ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ነፃ የሆነ ስፖርት እንዲስፋፋ በማድረግ በትክክለኛው መንገድ ተወዳድረው የሚያሸንፉ ጤናማ የሆኑ ውጤታማ ስፖርተኞች እንዲፈሩ የማስቻል ዓላማ ያለው ሲሆን ይህንንም ለማሳካት በየደረጃው ያለውን ግናዛቤ ማሳደግን አንዲሁም ምርመራና ቁጥጥርን ጨምሮ የተለያዩ ተግባርና ኃላፊነቶች ተሰጥተውታል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤታ የተቋቋመለትን ዓላማ እና በማቋቋሚያ ደንቡ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነቶች መሰረት በማድረግ በቋሚነት የሚጠቀምበትን ሎጎ በመቅረፅ ላይ እንገኛለን፡፡

ስለሆን በፅ/ቤቱ ሎጎ ውስጥ ለማካተት የተፈለጉትን ሐሳቦችና የመጀመሪያ ደረጃ የሆነውን የሎጎ Design ለአስተያየት ያረቀብን መሆኑን በታላቅ አክብሮት እየገለፅን ሁሉም አካላት የማሻሻያ አስተያየት እንዲሰጡበት በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

በፅ/ቤቱ ሎጎ ውስጥ ለማካተት የተሞከሩ ሐሳቦች፡-
 ሁለት አረንጓዴ ቅጠሎች፡- እያንዳንዱ አትሌት ተፈጥሯዊ በሆነ ችሎታው ተወዳድሮ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችልና እንደሚገባው ለመግለፅ ታስቦ የገቡ ሲሆን ቅጠሎች ከአንድ በላይ እንዲሆኑ የተደረገው የስፖርት አበረታች ቅመሞች በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ከፅ/ቤቱ ባሻገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ መረባረብና በእኩል ደረጃ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው ለማመላከት ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር አበረታች ቅመሞች በአብዛኛው የሚቀመሙበትን መነሻ ለማሳየት ያግዛል፡፡
 ክብና በውስጡ ጥቁር ቀለም የተቀባው ቅርፅ፡- በዋናነት የተከለከሉ አበራታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግ በመጠቀም ያልተገባ ውጤት ማስመዝገብና በስፖርቱ ውስጥ ማጭበርበር ተቀባይነት የሌለውና የተወገዘ ተግባር መሆኑ ለማሳየት የተቀመጠ ሲሆን ይህም ለቅጣት የሚዳርግ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከዚህ ባሻገር ክቡ ቅርፅ የስፖርት አበረታች ቅሞችን ወይም ዶፒንግ መከላከልና መቆጣጠር የአንድ ጊዜ ብቻ ስራ ሳይሆን ቀጣይነት ያለውና የሁሉንም አካላት ጥረት የሚጠይቅ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህም በተለምዶ Vicious circle የምንለው ነው፡፡ ከክቡ ጠርዝ ላይ ያሉት ነጭ መስመሮች በዋናነት አትሌቶችም ይሁኑ ሌሎች አካላት ከተከለከለውና ተቀባይነት ከሌለው እንዲሁም በጥቁር ቀለም ከተመሰለው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ወጥተው ተፈጥሯዊ በሆነ መንገድ ተወዳድረው ሲያሸንፉ ተቀባይነት ያለውና በሁሉም ዘንድ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን ለማመለካት ነው፡፡
 በክቡ ውስጥ ያለውና በምህፃረ-ቃል የተቀመጠውና ETH-NADO የሚለው ቃል፡- የፅ/ቤቱን የእንቅሊዝኛ ስያሜ በአጭሩ የያዘ ሲሆን ሲተነተን Ethiopia National Anti-Doping Office ይሆናል፡፡ የፅ/ቤቱ ስያሜ በምህፃረ-ቃል ጥቁሩ መደብ ላይ እንዲያርፍ የተደረገው ፅ/ቤቱ ከጥቂት ዓመታት በፊት የአገራችን ስፖርት በተለይም አትሌቲክሱ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ችግር ውስጥ በገባበት ጊዜ የተቋቋመ መሆኑንና ይህን ችግር በመከላከልና በመቆጣጠር ነፃ የሆነ ስፖርትን ለማስፋፋት እንደሚሰራ ለመጠቆም ነው፡፡ ምህፃረ-ቃሉ በአረንጓዴ ቀለም እንዲሆን የተደረገው ይህን ለማመላከት ነው፡፡

ከዚህ መነሳት ውድ ጊዜያችሁን ሰውታችሁ ለምትሰጡን ገንቢ አስተያየት ፅ/ቤታችን አስቀድሞ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *