በ2ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮ እና በ38ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ላይ የፀረ -ዶፒንግ Outreaching ኘሮግራም በባህር ዳር ተካሄደ።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን በ2ኛው የኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት አትሌቲክስ ሻፒዎና እና በ38ኛው የአበበ ቢቂላ ማራቶን ውደድር ላይ በአበረታች ቅመሞቸ ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የስፖርተኞችን ፣የስፖርት ባለሞያዎች፣የስፖርት ህክምና ባለሞያዎችን እዲሁም የስፖርቱን ባለሞያዎች ግንዛቤ ለማጎልበትና ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት በባህርዳር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም አካሄዷል፡፡
በዚህ የOutreaching ፕሮግራም በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ጥያቄና መልስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ለተሳታፊዎች ቲሸርትዎች፣ እስክሪቢቶዎች ፣ የፊት ማስኮች ተበርክቶላቸዎል በተጨማሪም በዶፒንግ ጽንሰ ሃሳቦችና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ መልዕክት የሚያስተላልፉ ብረሽሮች ተስራጭተዎል።
በአውትሪቺንግ ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ ማሰልጠኛ ማዕከላት የተውጣጡ በቀጣይ በአለም አቀፍ ደረጃ አገራቸውን ወክለው ለሚሳተፉ ተተኪ አትለሌቶች፣የትሌት ድጋፍ ሰጭ ባለሞያዎች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከተሰጡት ተግባራትና ሀላፊነቶች በየእርከኑ የሚገኙ ስፖርተኞችን፣የስፖርት ባለሙያዎች፣የስፖርት አመራሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማጎልበት ሀላፊነታቸውን እዲወጡ ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ የግንዛቤና የቅስቀሳ አውትሪቺንግ ኘሮግራም ሲሆን በበጀት አመቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል።