አትሌቶች በፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም ላይ በንቃት እየተሳተፉ ነው፡፡
መጋቢት 20/20l4 ዓ.ም፤ሐዋሳ ከተማ
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) ከመጋቢት19 ቀን እስከ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም ድረስ በሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኝው በ51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም ማካሄድ ጀመረ ፡፡
የOutreachingፕሮግራሙ ዋና ዓላማ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች፤ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎችን ግንዛቤ ለማጎለብት እና ሲፊ የህዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ንፁህ ስፖርትን ለማስፋፋት እዲሁም የስፖርቱ ማህበረሰብ በቂ ትኩረት እዲሰጥ ለማድረገረግ ነው፡፡
በዚህ የOutreaching ፕሮግራሙ፤ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች፤ ከክለቦች፤ከአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከላትና፤ ከተቋማት የተውጣቱ በርካታ በቀጣይ በአለም አቅም ደረጃ አገራችንን ወክለው የሚሳትፉ ተተኪ አትሌቶች፤የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ባለሞያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በስትራቴጂክ ዕቅዱ ከለያቸው ጉዳዮች አንዱ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች እንዲሁም የስፖርቱ ማህበረሰብ ግንዛቤ በቀጣይነት ለማጎልበትና የዶፒንግን ፅንሰ ሃሳቦች የተለዩ የማስተማሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስተማር ነው፡፡
በፕሮግራሙ የጥያቄና ውድድር የተካሄደ ሲሆን የተለያ፣ቲ-ሸርቶች፣የፊት ማስክዎች፣ እክሪበቶዎ፣ኩፊያዎች፣በራሪ ወረቀቶች፤ ተሰራጭቷል፣ በተጨማሪም በማይክ የፀረ-ዶፒንግ መልዕክት ተላልፏል፡፡