” የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በጋራ ማስወገድ (Together Against Doping) ” በሚል መሪ ቃል የግንዛቤና ንቅናቄ ፕሮግራም በመካሄደ ላይ ነው።
በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ባለው የ2ኛው ማሰልጠኛ ማእከላት የአትሌቲክ ውድድር ተሳታፊ አትሌቶች ፣የአትሌት ድጋፍ ሰጭ ስራተኛኞች “አበረታች ቅመሞችን በጋራ ማስወገድ” በሚል መሪ ቃል የግንዛቤና ንቅናቄ ፕሮግራም በድምቀት በመካሄድ ላይ ነው።
ለተንታና ደብረ ንብርሃን አትሌቲክስ ማስልጠኛ ማዕከላት አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የስፖርት ማዕከላትን፣ሰፖርተኞችን ፣የስፖርት ባለሞያዎችንና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ በማጎልበት ንፁህ ስፖርት እዲስፋፋ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።