የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-AdA) በሀዋሳ ከተማ በሚካሄደው 4ኛው የመላው የኢትዮጲያ የሴቶች ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ሴት ተተኪ ስፖርተኞች ፣ የስፖርት ባለሞያዎች እና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የትምህርት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሙ ከሚያዚያ 01-10/2014 ዓ/ም ድረስ ሲቆይ ታዳጊ ሴት ስፖርተኞች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እና ጤናማ ስፖርተኞች እንዲፈሩ ለማስቻል አላማ ያደረገ ፕሮግራም ነው፡፡
በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ የሚያስጨብጡ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ብሮሽሮች ፣ ቲሸርቶች፣ እስኪሪፕቶች እና ኮፊያዎች የተስራጩ ሲሆን እንዲሁም የተለያዩ አስተማሪ መልዕክት የያዙ ባነሮች ተዘጋጅተው በየውድድር ስፍራዎች ተሰቅለዋል ፡፡
በተጨማሪም በጥያቄ እና መልስ (Play True Quiz Computer Game) እና አዝናኝ በሆኑ ጨዋታዎች አማካይነት በዶፒንግ ዙሪያ ግናዛቤ ለመፍጥተ ተቸሏል፡፡
Previous post ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እደሚገባ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) አስታወቀ፡፡
Next post በኦሮሚያ ክልል በሰበታ ከተማ አስተደደር ስር ለሚገኙ ለአትሌቲክስ ክለብ አትሌቶችና ለአትሌት ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጣና ተሰጠ ፡፡