የጽህፈት ቤቱ (ETH-NADO) የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ እና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫ ያመላከተ የባለድርሻ አካላት የምክክር ጉባዔ፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት እስካሁን ድረስ ያለው አፈፃፀም እና ከጽ/ቤቱ ባህሪ አንፃር ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ምን መሆን አለበት? የሚለውን የሚያመላክት ስልት ለመቀየስ የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የምክክር ጉባዔ መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም በካፒታል ሆቴልና ስፓ አካሂዷል፡፡
የባለድርሻ አካላቱ የምክክር ጉባኤ ዋነኛ ዓላማ ጽ/ቤቱ ቀደም ሲል ጀምሮ በየደረጃው ሲካሄድ የነበሩ እንቅስቃሴዎችን በጥልቀት በመገምገም እና በአገር አቀፍ ደረጃ በመዘርጋት ላይ በሚገኙ የስፖርት የፀረ-አበረታች ቅመሞች የአሰራር ስርዓቶች ዙሪያ በመወያየት የጋራ የሆኑ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ባለድርሻዎች /Stakeholders/ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ መሆናቸውን እና ከሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ጽ/ቤቱ ወደተሻለ አሠራርና የአፈፃፀም ደረጃ ብቃት ለማሸጋገር /to build a confidence/ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የኢትዮጵያ የጠረጴዛ ቴኒስ ፌዴሬሽን በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ ያከናወኑትን ተግባራት ለሌሎች ፌዴሬሽኖች ተሞክሮ በሚሆን ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

የጋራ ውይይቱ በተለያዩ ጉዳዩ በሚመለከታቸው አካላት በልዩ ልዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በቀረቡት ገለፃዎችና ማብራሪያዎች ላይ የተለያዩ ጠቃሚ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይቱ በጥልቀት ተገምግሟል፡፡
በተያያዘ በዚሁ ዕለት በተካሄደውና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የውይይት መድረክ ተሳታፊዎች በመድረኩ መዘጋጀት የተደሰቱ መሆናቸውና እንዲሁም በአጠቃላይ በውይይቱ ሂደት የረኩ መሆናቸውን መገንዘብ ተችሏል፡፡
በመድረኩ ላይ የስፖርት ማህበራት ተወካዮች፣ የስፖርት ማዕከላት፣ የሙያ ማህበራት፣ የስፖርተኞች ተወካዮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት እና ከሌሎች ጨምረው የመጡ ከ100 በላይ ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

ዜናውን ያጠናቀረው የ ጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *