የፀረ-ዶፒንግ የግንዛቤና የህዝብ ንቅናቄ (outreaching) ፕሮግራም በ10ኛው የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች እና 3ኛው ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ውድድር በአሰላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ፡፡
ቀን፡ የካቲት 28/2014 ዓ.ም
ከየካቲት 28 – መጋቢት 04/2014 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ውድድር ላይ ከአትሌቲክስ ተወዳዳሪዎች በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል 5ኛው የሴቶች ውድድር ተሳታፊዎች እና የ2014 ዓ.ም ከ20 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተወዳዳሪዎች በግንዛቤና በንቅናቄው እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች እየተደርገ ሲሆን አሳታፊ የሆኑ አትሌቶችን በቀላሉ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችል የጥያቄና መልስ ውድድር የቅስቀሳና ፕሮሞሽን ማቴሪያሎች ፤ ብሮሸሮች ፣ የፊት ማስክዎች፤ ለስፖርተኞች ፣ ለስፖርት ባለሞያዎች፣ለስፖርት አመራሮችና ሌሎችንም ተሳታፊዎች ተሰራጭቷል፡፡
በተጨማሪ የተለያዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ባነሮች ተዘጋጅተው ለዕይታ በሚያመች ቦታዎች እንዲሰቀሉተደርጓል:: ፕሮግራሙ ለቀጣይ ቀናቶችም የሚቀጥል ይሆናል