የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና ንቅናቄ የመፍጠር የOutreaching ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ ፡፡
ህዳር 29/2017 ዓ.ም
ሱሉልታ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ካሉት ዋነኛ ተግባራት አንዱ የስፖርተኞች እና የስፖርት ባለሙያዎች በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው በማድረግ ውጤታማ እና ጤናማ የሆኑ ስፖርተኞች እንዲሁም ፍትሃዊ የሆነ ስፖርታዊ ውድድር በሀገራችን እንዲኖር ለማስቻል በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች በሚካሄዱ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመገኘት በስፋት የግንዛቤ የማሳደግ ስራ እየሰራ ይገኛል ፡፡
በዛሬውም ዕለት ኦሮሚያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አዘጋጅነት ከህዳር 27_29/2017 ዓ.ም በሱሉልታ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው 1ኛ ዙር የኦሮሚያ የስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከላት ውድድር ተሳታፊ ስፖርተኞች እና የስፖርት ባለሙያዎችን በማሳተፍ በፀረ-አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ በማሳደግ እና ንቅናቄ በመፍጠር የOutreaching ፕሮግራም በስፋት በማካሄድ በዛሬ ዕለት ተጠናቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *