ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እደሚገባ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) አስታወቀ፡፡
’’አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በመጠቀም ለማሸነፍ መሞከር ውጤቱ ጊዜያዊ ነው፡፡ ተፈጥሮአዊ ውጤት አይደለም፡፡ በማጭበርበር መሆን የለበትም ፡፡’’ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ
የኢትዮጵያፀረ-አበረታችቅመሞችባለስልጣን(ETH-ADA) በስፖርትቱ ዘርፍ ተግዳሮት እየሆነ የመጣውን ዶፒንግን እዲሁም በዜጎች ላይ የጤና፤ የበማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኘውን ዶፒንግን ከመሰረቱ ለመከላከል ለመቆጣጠር ከአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከ ፍተኛ አመራሮች፤ ከስፖርት ፌድሬሽን ፕሬዝዳንቶችና ከማሰልጠኛ ማዕከላት ዳይሬክተሮች ጋር መጋቢት 26 ቀን 2014 ዓ.ም በአራት ኪሎ ወጣት ማዕከል የመሰብሰቢ አዳራሽ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአዲስ አበበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ እደተናገሩት የውይይቱ ዓላማ አበረታች ቅመሞች ከመከላከልና ከመቆጣጠር አኳያ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ፤ ጉዳዩ በቂ ተትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ እዲሁም ሁላችንም በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ቢኖረንም ማስታወስ በማስፈለጉ እደሆነ ገልጸው ተሳታፊዎች ውይይቱን በትኩረት እዲከታተሉ አደራ በማለት መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
የመከፈቻ ንግግሩን ተከትሎ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋነታዬ ገዛኽኝ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በአገር አቀፍ ደረጃ አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ንፁህ ስፖርትን በማስፋፋት ረገድ ሰፊ ሚና እንደሚጫወቱ ይታመናል፡፡ አበረታች ቅመሞች በአንድ ተቋም በቻ የሚቀረፍ አይደለም በየደረጃዉ የሚገኙ አካለትን ቅንጅታዊ አሰራርን ይጠይቃል ፤በአገራችን ስፖርት ላይ የሚታየውን የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ችግር እንዲቀለበስ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅ ኃላፊነት እደሆን ገልፀዋል፡፡
ዶፒንግ የማህበረሰብ የጤና ችግር ነው፡፡ በመሆኑም በየደረጀው ያሉ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባቸዋል፤የፀረ-ዶፒንግ ጉዳይ በመዋቅራችው ውስጥ አካቶ ተግባራዊ ማድረግ ተጠናክሮ መቀጠል እዳለበት አሳስበዋል፡፡
በዕለቱ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አሰራር፣ አደረጃጀት እና ህጋዊ ማዕቅፎ የፀረ-ዶፒንግ እንቅስቃሴው፤ በተመለከተ እዲሁም የአዲስ አበባ ወጣጦችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊነት ምን መሆን አለበት በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይትም ተደርጎበታል፡፡
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ እደተናገሩት ዋናው ግንዛቤ መፍጠር ነው፤በዚህ ላይ ቢሮው እየሰራ ነው፡፡ የዶፒንግን ተፅዕኖ ሁላችንምመገንዘብአለብን፤የስፖርት ባለሞያው፣ ቤተሰብዜጋው፣ኃኪሙ ኃለፊነት አለብን፤ ተልኮውን ወስደን በመድረኮች፣በፌስቲባሎችላይ የተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴዎች በመጠቀም ግንዛቤ መፍጠር አለብን፡፡በደንብ ተባብረን ከሰራን ውጤት ማምጣት እደሚቻል አስረድተዋል፤
በመጨረሻም ዋና ኃላፊው አቶ አብረሃም በጋራ እንስራ፤የሚፈለግብን እንወጣ ብለዋል፡፡ቢሮው የሚካሄዱ የንቅናቄ ቬስቲባሎችን በበጀትም ሆነ በፕሮግራምም መደገፍ እንችላለን፡፡
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የቢሮው ም/ዋና ኃላፊ አቶ ዳዊት እዳሉት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ወደዚህ መጥጠታችው እድሉን ሰለሰጣችውን ምስጋ አቀርባለው፤በቀጣይ በግምገማ እንገናኛለን በማለት መድረኩ ተጠናቋል፡፡