ዶፒንግ የሚያደርሰው ኪሳራ ከፍተኛ በመሆኑ አትሌቶች ከዚህ ሊጠበቁ ይገባል ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳሬክተር አቶ አንበስ እንየው::
የካቲት16/2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-ADA/ ለኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ታዳጊ አትሌቶችና አመራሮች በዛሬው እለት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳሬክተር አቶ አንበሳው እንየው በመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደተናገሩት ዶፒንግ በአትሌቶች ላይ ከሚያስከትለው ውስብስብ የጤና መታወክ በተጨማሪ በአገርም ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ ከፍተኛ በመሆኑ ታዳጊ አትሌቶች ስለዶፒንግ በቂ ግንዛቤ መያዝ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
ተቋማችን በዶፒንግ ጉዳይ ላይ በትኩረት እየሰራ የሚገኝ በመሆኑም አትሌቶቻችን ለስፖርታዊ ስነ-ምግባሮች ተገዢ በመሆን ዶፒንግን የሚጠየፉ ውጤታማ አትሌቶች በመሆን የአገር ኩራት ሊሆኑ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ፡፡
በመጨረሻም ለስፖርተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ በማዘጋጀቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱን አመስግነው ታዳጊዎች ይህንን አጋጣሚ በደንብ በመጠቀም ስለ ዶፒንግ ያላቸውን ግንዛቤ ማሳደግ ይገባቿል በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ፡፡
የኢ/ፀ/አ/ቅ/ባ/ት/ስ/ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈለቀ ዋለልኝ በበኩላቸው ዶፒንግ ትውልድን የሚያቀጭጭ የስፖርት ችግር በመሆኑ ተቋማችን በዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር መከላከልና መቆጣጠርን አላማ አድርጎ እየሰራ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡
አያይዘውም ተቋሙ ተደራሽ ለመሆን የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የዶፒንግን ጉዳይ በትምህርት ካሪኩላም ውስጥ በማካተት እንዲሁም ማሰልጠኛ ተቋማት በስልጣና ማኑዋሎቻቸው አካተው እንዲሰጡ በስፋት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል ፡፡
ስልጠናው በትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆኑ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምንነትና መሰረታዊ ጉዳዮች ፣ በሚያስከትለው ጉዳት ፣ በዶፒንግ ህግ ጥሰት ፣ በሰራር ስራዓቶች ዙሪያ እና በሌሎች ገለፃ ተደርጓል ፡፡
በመጨረሻም ከስልጣኞች ጥያቄ እና አስተያየቶች ተነስተተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
                                                ዶፒንግን በጋራ እንከላከል!!!