ህገ ወጥ የሆነ አካል በህግ አግባቡ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰደ ይገባናል፦ የኢትዮጰያ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል
ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጰያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከፌዴራል ዓቃቢ ህግ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ፍትህ አካላት ለተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች መድረክ ላይ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ሰነዶች ቀርበው ከተሳታፊዎች ጋር በስፋት ውይይት ተካሄዷል ፡፡
የኢትዮጰያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ ላይ እንደተናገሩት ፡-
በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ የወንጀል ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ ብዙ ርቀት ተጉዘን መሥራት አለብን። ይህ መድረክ ከጉዳዩ ባለቤቶች ጋር ወይም ፈፃሚ አካላት የውይይት መድረክ እንጅ የባለድርሻ አካላት ውይይት አይደለም ። የህግ ማዕቀፎች ተግባራዊ የሚደረገው በሕግ አካላት ነው። አበረታች ቅመም ሀገራችን ውስጥ ካሉ አበይት ችግሮች ውስጥ አንዱ በመሆኑና ከዚህ ችግር በዘላቂነት እንዴት መወጣት እንዳለብን በጋራ ተቀናጅተን መስራት ይኖርብናል።
ሀገራችን አበረታች ቅመሞች ጋር እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎች በመጀመሪያ ስፖርተኞች በብዛት አበረታች ቅመሞችን የመጠቀም ልምዱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የመጣበት ሁኔታ መኖሩ እና በሁለተኛ በደላሎች ከአትሌቶች፣ አንዳንድ ስነምግባር የጎደላቸው የፈርማሲና ህክምና ተቋማት ጋር በመሆን በዜጎች ላይ ጉዳት እያደረሱ በመሆኑ ደላሎችን መቆጣጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል ።
ክቡር ዳይሬክተሩ አክለውም ህገ ወጥ የሆነ አካል በህግ አግባቡ አስፈላጊውን እርምጃ መወሰደ እንደሚገባ እና ስራዎችን ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።