ለህክምና ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ።
ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የስፖርት ህክምና ባለሙያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በዋናነት ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና የአሠራር ስርዓቶች እንዲሁም በምርመራና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።