የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግና ንቅናቄ ለመፍጠር ሲካሄድ የቆየው የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም ተጠናቀቀ፡፡
ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ሲካሄድ የቆየው የታዳጊ ወጣቶች የቦክስ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ስፖርተኞችና ለስፖርት ማህበረሰቡ ሲካሄድ የቆየው የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና ንቅናቄ የመፍጠር የOutreaching ፕሮግራም በስፋት በማካሄድ በዛሬ ዕለት ተጠናቋል፡፡
በኘሮግራሙ ላይ ሰፊ ስራዎችን መስራት የተቻለ ሲሆን በዚህም የስፖርቱ ባለሙያዎች ከስፖርት አበረታች ቅመሞች ራሳቸውን መጠበቅ የሚችሉበትን ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል፡፡