በፔሩ ሊማ በሚካሄደው የ20ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌትክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፉ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከኦገስት 27-31/2024 በፔሩ- ሊማ በሚካሄደው የ20ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌትክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ ለሚሳተፉ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናው በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን መሰረታዊ ጽንሰ ሀሳቦች ፣ የተከለከሉ ንጥረ ነገሮች እና ዜዴዎች ፣ በአሰራር ስርአቶች፣ የሚያስከትለውን ጉዳት እና ባሉት ሕግና ደንቦች እንዲሁም በምርምር እና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ ያተኮረ ነበር።