በስፖርት አበረታች ቅመሞች(ዶፒንግ) እና በታያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለመብራት ኃይል አትሌቲክስ ክለብ ስፖርተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ::
ቀን-ዕረቡ 24/2012ዓ.ም
ቦታ ፡-መብራተ ኃይል ስፖርት ክለብ አዳራዲሽ አዲስ አበበ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ለኢትዮጵያ መብራት ኃይል አትሌቲክስ ክለብ ሰልጣኞች በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በክለቡ አዳራሽ ጠሰጥቷል፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫው የተካሄደው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤መርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ የዶፒንግ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶች እና በሚያሰከትሉት ጉዳቶች ላይ ያተኩረ ነው፡፡
በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዲሬክተር አዝጋጅነት ነው ትምህርቱ የተሰጠው ፡፡
የመድረኩ ተሳታፊ የሁኑ አትሌቶች በፀረ-ደፒንግ ዙሪያ የተሰጠው ስልጠና ጥሩ ግንዛቤና እውቀት እዳገኙበት ገልፀዋል፡፡
ስልጠናው የሰጡት በጽ/ቤቱ የትምህርት፣ስልጠናና ምርምር ዲሬክቶሬት ዲሬክትር በሆኑት አቶ ክፍሌ ሰይፈ ሲሆኑ፡፡ በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳዮቹ ዙሪያ ሰፊና ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ 120 አትሌቶች ተካፋይ ሆነዋል፡፡