በስፖርት አበረታች ቅመሞች(ዶፒንግ) እና በታያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ለሰፖርት አካዳሚና ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኛች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነወ፡፡

ቀን- ህዳር 9/2012 ዓ.ም

ቦታ- አዳማ ከተማ መኮንን አዳማ ሆቴል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በአዳማ ከተማ ከህዳር 9-10/2012 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በፀረ-አበረታች ቅመሞች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለስፖርት አካዳሚና ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች በመሰጠት ላይ ነው፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫው የሚካሄደው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤መርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ የዶፒንግ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶች እና በሚያሰከትሉት ጉዳቶች ላይ እንዲሁም በሰፖርት የሚወሰዱ ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (Supplements) ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡

ሂደቱ /Awareness Creation Training/ ሲሆን፣ በተዘረጋው እቅድ መሰረት ስልጠናው ከሚጀምርበት እስክ ሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ በገለፃ /Lecture/ እና የቡድን ውይይት /Group Discussion/ የሚካሄድ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዲይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ስልጠናው የተዘጋጀበት ዋና ዓላማም ስፖርተኞች በስነ-ምግባርና በክህሎት ለመቅረጽ የዜግነትና ሙያዊ ኃላፊነት የተጣለባችው የሰፖርት አሰልጣኞች ዶፒንግን በዘላቂነት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ለሚደረገው ጥረት ትኩረት ተስጥቶ የመደገፍና የማሳወቅ (Advocacy) ስራዎች መስራት፤ በተለይ የስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ድረሻ የላቀ መሁኑን ከማስቻል አኳያ ከፈተኛ ኃላፊነት እዳለባቸው አስተውቀዋል፡፡

በተጨማሪ ጽ/ቤቱ የዶፒንግን የሚመለከቱ ጉዳዮች በስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ካሪኩለም ውስጥ እዲካተት ገንቢ አሰተያየቶችን እንድታበረክቱ ግንዛቤ እዲኖራችው ለማድረግ መሆኑን ዋና ዲይሬክተሩ አያይዘው ገልፀዋል ፡፡
በመጨረሻም ዋና ዲይሬክተሩ አቶ መኮንን ይደርሳል ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት መከታተል እዳለባቸሁ መልክት በማስተላለፍ ስልጠናዉን በይፋ አስጀምረዋል፡፡

ስልጠናው የሚሰጡት በጽ/ቤቱ የትምህርት፣ስልጠናና ምርምር ዲይሬክቶሬት ዲይሬክትር በሆኑት አቶ ክፍሌ ሰይፈ ሲሆኑ፡፡ በእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳዮቹ ዙሪያ ሰፊና ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን ትኩረቱም የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (Supplements) መሆኑ ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *