በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ስር ለሚገኙ ክለቦች፤ለፕሮጄክትና ክፍለ ከተማ አትሌቲክስ አሰልጣኞች የስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplments) ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጋር ያላቸው ግኑኝነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

አርብ ህዳር 11/2013 ዓ.ም /አዲስ አበባ ወጣቶች ስፖርት ማዕከል (ወወክማ)/ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን/EAF/ በጋራ በተዘጋጀ መድርክ ላይ በአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ስር ለሚገኙ ከለቦች፤ ለፕሮጄክትና ክፍለ ከተማ አሰልጣኞች ‹‹የስፖርት ድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦች (Supplments) ከአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ጋር ያላቸው ግኑኝነትና በተያያዥ ርዕሶች›› ላይ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡በስልጠናው ላይ ከ80 በላይ ተሳተፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው የተዘጋጀው በጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ሲሆን፤
ትምህርቱን የሰጡት ወ/ሪት ቅድስት ታደሰ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ከፍተኛ የህክምና ባለሞያ ናቸው፡፡ የትምህርቱ ትኩረት የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ምንነት፤ የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ጋር ስላላቸው ግኑኝነት፤ከአሰልጣኝና ከአትሌቱ ምን ይጠበቃል በሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ነው፡፡

ባለሞያዋ አያይዘው እንደገለጹት የስፖርት ድጋፍ ሰጭ ነጥረ-ነገሮች (Supplments) ለአበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ሊያጋልጡ ይችላሉ፤ አትሌቶች ማንኛውም ድጋፍ ሰጭ ምግቦችን ከመጠቀማቸው በፊት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በተጨማሪም የአትሌቲክስ አሰልጣኞች የፀረ-ዶፒንግ ፎረም መቀጣይ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር ወይይት ተደርጓል፡፡

የዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ(WADA) ከፊታችን ጥር 2021 ጀምሮ የፀረ-ዶፒንግ ህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አካላት ላይ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ መመሪያ ማውጣቱን <<የዶፒንግ ሕግ ጥሰት የፈፀመ አትሌት፤ አትሌቱን ጨምሮ አትሌቱ የወከለው አገርና ብሔራዊ ፌድሬሽኖችን ከማንኛዉም ኢንተርናሽናል የውድደር ተሳትፎ እንደሚያሳግድ >> ባለሞያዋ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *