አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የስፖርት መምህራን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቆመ፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተወጣጡ መምህራን በሆሳዕና ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ለተወጣጡ የስፖርት ሳይንስ መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በስፋት ሲሰጥ ቆይቷል።
በአሁኑ ሰዓትም ለአምስተኛ ዙር በተዘጋጀው መድረክ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን የስፖርት መምህራን ችግሩን በዘላቂነት በመቅረፍ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንደሚጫወቱ አረጋግጠዋል።
Previous post ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አመራሮችና ለስፖርት ባለሞያዎች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤና ውይይት ፕሮግራም ተካሄደ፡፡
Next post የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የሆነው አሌክስ ተሰማ ሐይሌ የፀረ-አበረታች ቅመሞች የህግ ጥሰት ፈፅሞ በመገኘቱ የማስጠንቀቂያ ቅጣት ተላልፎበታል።