አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የስፖርት መምህራን ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተጠቆመ፤ ከተለያዩ አካባቢዎች ለተወጣጡ መምህራን በሆሳዕና ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ከኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ለተወጣጡ የስፖርት ሳይንስ መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በስፋት ሲሰጥ ቆይቷል።
በአሁኑ ሰዓትም ለአምስተኛ ዙር በተዘጋጀው መድረክ የግንዛቤ ማሳደጊያ ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን የስፖርት መምህራን ችግሩን በዘላቂነት በመቅረፍ ረገድ የሚጠበቅባቸውን ገንቢ ሚና እንደሚጫወቱ አረጋግጠዋል።

By Ermias