የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 400/2009 በይፋ የተቋቋመ ሲሆን ሁሉም ስፖርቶች ከአበረታች ቅመሞች የጸዱና እና ነፃ የሆኑ የሰፖርት ውድድሮች ሊተገበሩ ይገባል ብሎ ያምናል፡፡ የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴን በተለያዩ አካባቢዎች ወጥ በሆነ መንገድ ተግባራዊ በማድረግ ሁሉም የስፖርት አይነቶች አበረታች ቅመሞችን የሚዋጉበትን መንገድ ያበረታታል፡፡
የፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴዎችን በመተግበር ላይ ያተኮሩ አጠቃላይ የስፖርት አቀራረብን አስፈላጊነት እና የመልካም ስፖርት ጥሩ መንፈስ ጥሰትን መከላከል የኢትዮያ ብሔራዊ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የባለፉት የስኬት ዓመት ነበር፡፡
በተለይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት የፀረ-ዶፒንግ ስልጠናን፣ ትምህርትን፤ ምርመራና ምርምር ማድረግ እና ማህበራዊ ንቅናቄዎችን በብቃት ማከናወን ላይ ትኩረት አድርጓል:: እንዲሁም እንደ ህክምና ፍቃድ አስጣጥ ፣ የውጤት አስተዳደር እና የህግ ጉዳዮችን መስማት( Hearing) ያሉ የተለያዩ አሰራሮችን እና ስርዓቶችን በማጠናከር ፤ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ስራ አመራር እና አስተዳደር ስርዓትን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም እንደ አለም አቅፉ አትሌቲከስ ፌዴሬሸኖች ማህበር፣ ከዓለም አቀፍ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጅንሲ እና ከሀገር ውሰጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነቶችን ማጠናክር ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡