የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት ከኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከሁሉም ክልሎች/የከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የስፖርት ባለሞያዎች(አሰልጣኞች፣ ዳኞች እና ኢንስትራክተሮች) በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ መስጫ ስልጠና እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡
የስፖርት ባለሞያዎችም የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን የመደበኛ ስራቸው አካል በማድረግና በትምህርትና ስልጠና ካሪኩለሞቻቸው ውስጥ በማካተት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይም ስልጠናው ፅ/ቤታችን በታዳጊ ወጣቶች ፕሮጀክት ደረጃ የስፖርተኞችን እውቀትና ግንዛቤ ለማጎልበት እየተዘረጋ ያለውን የመሰረታዊ ትምህር (Value Based Education) በአግባቡና ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
ETH-NADO provides awareness creation training for athlete support personnel (Coaches, Referees, Instructors, etc) represented from regions and city administrators in-collaboration with FDRE Sport Commission. This training will be very much valuable to effectively implement the Anti-Doping Value Based Education at the youth training project level.