በሁለተኛው ዙር የስልጠና መርሃ-ግበር ለተካተቱ የስፖርት አካዳሚና ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች በአበረታች ቅመሞች ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡

የኢትዮጵያ በሔራዊ ጸረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በሁለተኛው የፀረ-ዶፒንግ የስልጠና መርሃ ግብር ለተካተቱ የስፖርት አካዳሚና ማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

ሥልጠናው የሚቆየው ከታህሳስ 1 እሰከ 2/2012 ዓ.ም ሲሆን፤ የስልጠናው ዋና ዓላማ የስፖረት አካዳሚና ማስልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች በፀረ-ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤአችሁን በማሳደግ ያገኛችውትን ዕውቀት በማሰልጠኛ ተቋማት ካሪኩለም ውስጥ አካታችው ማስተማር የሚያስችላቸውን እውቀት ለማስጨበጥ እደሆነ ተገልፃል፡፡

ሁለተኛው ዙር የስልጠና መርሃ ግብር መክፈቻ ላይ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት ወ/ሮ ፋንታዮ ገዛኽኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ፀረ- አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዲሬክተር ግንዛቤ በማሳደግ የበኩላቸውን ድርሻ እድትወጡ እደሆነ ገልጸዋል ፡፡
እናንተም ወደስልጠና ተቋማቻው ስትመለሱ በስልጣና እቅዳችው ውስጥ አካታችሁ የዶፒንግን ጉዳይ ማስተማር ይጠበቅባችዋል ፡፡የዛሬው ስልጠና የሚሰጣችውን ተልዕኮ ለመወጣት ትልቅ አስተዋፆ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ለሁለት ቀን በሚቆየው በዚህ ስልጠና በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤መርመራና ቁጥጥር ሂደት፤ የዶፒንግ የተለያዩ የአሰራር ሥርዓቶች እና በሚያሰከትሉት ጉዳቶች ላይ እንዲሁም በሰፖርት የሚወሰዱ ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (Supplements) ዙሪያ የሚያተኩር ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *