ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ባከናወናቸው ስራዎች ዙሪያ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
ነሐሴ 28/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ  የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን በ2017 በጀት አመት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያከናወናቸው  አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና የአበረታች ቅመሞችን ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫ ላይ  የተነሱ ዋና ዋና ሐሳቦች እንደሚከተለው ቀርቧል።
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2ዐ17 ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸው ስራዎች ውስጥ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ንጽህ ስፖርት ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን  በማከናወን በበጀት ዓመቱም ውጤታማ እንቅስቃሴዎች ማካሄዱ ተገልጿል።በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በ2ዐ17 ዓ.ም በጀት አመት ያከናወናቸው ስራዎች ውስጥ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ንጹህ ስፖርት ለማስፋፋት የስፖርቱ ማህበረሰብ  የግንዛቤ ለማሳደግ አጫጭር እና የገልፅ ለገጽ ስልጠናዎችን በመስጠት 4488 የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ መደረጉን እና በህዝብ ንቅናቄ ዘመቻ ለማዳረስ  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በአወትሪችንግ ኘሮግራም እና በህዝብ ንቅናቄ ፕሮግራም  የማህበረሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር እንደተቻለም ዳይሬክተሩ  ጠቁመዋል፡፡
በሌላው በኩል በትምህርት ቤቶች በመደበኛ ትምህርት እየተማሩ ያሉበት ሁኔታ መኖሩና በፀረ አበረታች ቅመም በቂ የሆነ ግንዛቤ ይዞ እንዲወጡ ለማድረግ አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ በመሆኑ በ2017 በመደበኛ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ አበረታች ቅመም ጉዳይ ተካቶ ለሁሉም ዜጎች እየተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
አያይዞም ትምህርት እና ስልጠና ሥራዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት ኢ-መደበኛ ኘላት ፎርም ተዘርግቶ ስፖርተኞች ስልጠናውን ተከታትሎ መመረቃቸው ገልፀዋል።
በተጨማሪም በዶፒንግ የበለጠ ተጋላጭ የሆኑ ስፖርቶችን በጥናት በመለየት በውድድር ጊዜና በውድድር ጊዜ ውጪ 1196 የሚሆኑ ምርመራዎች የተደረገ መሆኑ እና ሙያተኞችንም የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቶ በበጀት አመቱ ውጤታማ የሆነ የምርመራና ቁጥጥር ስራ መሰራቱ ገልፀዋል ።
አትሌት ባዮሎጂካል ፓስፖርት በአለም አቀፍ ደረጃ ይፋ የተደረገ ኘሮግራም ሲሆን እንደ ሀገር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጥብቅ ዲሲፕሊን የአትሌቶች ኘሮፋይል በማጥናት በየጊዜዉ ያላቸው ብቃት በማጥናት አበረታች ቅመም መጠቀም አለመጠቀማቸው የተረጋገጠበት ሳይንሳዊ የሆነ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ መደረግ የተቻለ ኘሮግራም በሚፈለገው ደረጃ በትኩረት የተሰራበት በጀት አመት መሆኑን ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።
አለም አቀፍ ግንኙነትን የማጠናከር ሥራ በስፋት የተሰራ መሆኑና በአለምአቀፍ ተቋማትም የሀገራችን እንቅስቃሴ ጤናማ ግንኙነት የተጠናከረና አቻ ተቋማት ጋር ቀጣይነት ባለው መንገድ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ክቡር ዳይሬክተሩ ገልፀዋል ።
የቶኪዮ አለም አቀፍ ውድድር ተሳትፎ ለማድረግ የተቀመጡ መስፈርቶች ለሟሟላት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ሲሆን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተለዩ 143 የሚሆኑ ስፖርተኞችን በአለም አቀፍና በሀገራችን የምርመራ ቋጥ ውስጥ በማስገባት ከጥር 2017 ጀምሮ ምርመራ እየተደረገ መሆነኑን አሳውቀዋል።
ኢንተለጀስ እና ኢንቪስቲግሽን ስራዎች አጠናክረን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት አስፈላጊው እርምጃ  የተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የምርመራና ቁጥጥር ስራዎችንን አጠናክሮ እንደሚቀጥሉ ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ጠቁሟል።
አያይዞም የህግ ጥሰት የፈፀሙ አካላት በ2017 በጀት አመት የተከለከሉ አበረታች ቅመም በመጠቀም በተለያየ ደረጃ ህግ ጥሰው የተገኙ አትሌቶች አበረታች ቅመም በመጠቀም 3 አትሌቶች ላይ አስፈላጊ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱና ከመጠቀም ባለፈ በሌሎች ህግ ጥሰት ላይ የተሳተፉ አትሌቶች አንድ የምርመራ ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ባለመሆንና ሌላኛው አትሌት አድራሻ ምዝገባ ግዴታ ባለመወጣት አስተዳደራዊ እርምጃ የተጣለባቸው መሆኑ ገልፀው በአጠቃላይ በበጀት አመቱ 5 አትሌቶች አበረታች ቅመም በመጠቀምና ሌሎች የህግ ጥሰት በመፈፀም አስተዳደራዊ ቅጣት የተጣለባቸው መሆኑ አሳውቀዋል ።
በመጨረሻም በ2017 በጀት አመት አጠቃላይ እቅድ አፈፃፀማችን ጥሩ የሆነ እንቅስቃሴ የተደረገበትና የአለም አቀፍ ደረጃ ጥሩ የሆነ እይታ ማግኘት የተቻለበት መሆኑን ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመግለጫቸው ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *