ተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት ጥቅል እቅድ አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ግምገማ አካሄደ።
ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም
አዳማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም ጥቅል የተቋሙ እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ፣ የ2017 በጀት አመት የክትትል እና ድጋፍ ግብረ መልስ እና የ2018 በጀት ዓመት የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ እንዲሁም አዲሱ የሲቪል ሰርቪስ አዋጅና መመሪያ ላይ የተቋሙ አመራሮች እና አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በአዳማ ከተማ የጋራ ውይይት አካሄዷል ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል በመድረኩ ካስተላለፊት መልዕክት በ2017 እቅድ አፈፃፀማችን የነበረው አጠቃላይ እንቅስቃሴ በጥልቀት በማየት የነበሩን ክፍተቶች እና ጥንካሬዎችን በመፈተሽ የነበሩብንን ክፍተቶቻች በመሙላት ጥንካሬዎችንን አጠንክረን ይዘን ለቀጣይ በ2018 በጀት አመት በጥልቀት በመወያየት ጥሩ አቅም የምንፈጥርበት የውይይት መድረክ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
አክለውም በ2017 በጀት አመት በትምህርትና ስልጠና ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ የስልጠናና የውይይት መድረኮች፣ የአውት ሪችንግ እና የህዝብ ንቅናቄ ሥራዎችንም ስኬታማ በሆነ መንገድ እንደተከናወነ ገልጿል።
በአበረታች ቅመሞች በህግ ማዕቀፍ በአሰራሮች ዙሪያ የስፖርት ማህበረሰብና ከስፖርት ውጪ ያሉ ባለድርሻ አካላት አጠቃላይ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ማድረግ መቻሉ ዳይሬክተሩ ተናግሯል።
በውድድር ጊዜ ምርመራና ከውድድር ጊዜ ውጪ 1196 በላይ ምርመራዎች በመስራት እና ለቶክዮ አለም ሻምፒዮና ስፖርቶኞችን ዝግጁ በማድረግ እንደ ተቋም ውጤት ማስመዝገብ የተቻለበት በጀት አመት መሆኑ ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል።
በመቀጠል የህግ ጥሰት የፈፀሙ አካላትን አግባብነት ያለው አስተዳደራዊ እርምጃ የወንጀል ተጠያቂነት ከማረጋገጥ አኳያ የተሰሩ ስራዎች እንዳሉ ተናግረዋል።
የኢንተለጀንስና ኢንቨስቲጌሽን ሥራችን መስራት የጀመርነው ካለፈው 2016 በጀት አመት ጀምሮ በሚፈለገው ደረጃ የዳኝነች ስርአቱንና ህግ የማስከበር ስርአቱ እየተጠናከረ በመምጣቱ የወንጀል ተጠያቂነት ለማረጋገጥ ጥረቶችን እየተደረገ መሆኑና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በማስተባበር አበረታች የሆነ ውጤቶችን የታየበት መሆኑ ገልፀዋል።
በመጨረሻም በድጋፍና ስራ አመራር የሥራ ክፍሎቻችን የተቋሙ ተልኮ እንዲሳካ ከማድረግ አኳያ የተሰሩ ሥራዎች በጣም የሚያኮሩ መሆናቸውን አቶ መኮንን ተናግረዋል ።
በመድረኩም የ2017 በጀት ዓመት ጥቅል እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ፣ የክትትል እና ድጋፍ ግብረ መልስ እና የ2018 በጀት ዓመት የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ እንዲሁም በፌዴሬል መንግስት ሠራተኛች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መመሪያ በውጤት አስተዳደር ህግ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ በአቶ ንጋቱ መኮንን አማካኝነት ሰነዶች አቀርቧል ።
በቀረቡ ሰነዶች ከሰራተኛው ጥያቄ ና አስተያየት ቀርቦ በሚመለከታቸው ስራ ክፍሎች እና ከበላይ አመራሮች ሰፋ ያለ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበታል ።