ለመከላከያ ስፖርት ክለብ አትሌቶች በዶፒንግ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ::
ቀን፡-ጥቅምት 18/2013ዓ.ም
ቦታ፡- መከላከያ ስፖርት ክለብ አዳራሽ / ጃን ሜዳ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት /ETH_NADO/ ለኢፌድሪ መከላከያ ስፖርት ከለብ አተሌቶች በአበረታች ቅመሞች ወይም በዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳብና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፡፡ 100 ያህል አትሌቶች ስልጠናዉን ተከታትለውታል፡፡
በስልጠና መድረኩ የመክፈቻ ሥነ-ሥርአት ላይ ንግግር ያደረጉት ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጸረ-አበረታችቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እዳሉት ጽ/ቤቱ በየደርጃው ህብርተሰቡንና በተለይም የስፖርቱን ማሀበረሰብ በዶፒንግ እና በስፖርቱ ውስጥ የሚያስከትላቸውን ጉዳቶች ዙሪያ ለማስተማር የሚያስችሉ የተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞች ቀርፆ፤ ተግባራዊ በማድረግ ላይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪየ ግንዛቤ ማስጨበጥ ነው፡፡በቀጣይ ትምህርትና ስልጠናው ተጠናክሮ እደሚቀጥል ም/ ዋና ዳይሬክተሯ ገልጸው፤ የተዘጋጀውን ትምህርት በትኩረት አዲከታተሉ አሳስበው መድረኩን አስጀምርዋል፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤ምርመራና ቁጥጥር ሂደት ዙሪያ በጽ/ቤቱ ትምህርት፤ስልጠናና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች ገለጻ ተደርገዋል፡፡
በመጨረሻም ከተሳታፊዎች በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ተደርጓል ፡፡
ስልጠናው በሁለት ዙር ተከፋፍሎ የሚሰጥ ሲሆን፡፡ ለሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች አርብ ጥቅምት 20/2013 ዓ.ም ስልጠና እደሚሰጥ ታውቋል፡፡
እራሳችንን ከአበረታች ቅመሞች እንጠብቅ!!