ለማሰልጠኛ ተቋማት በዶፒንግ ላይ የሚሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እደቀጠለ ነው ፡፡
የዛሬው የ4ኛ ቀን ፕሮግራም
ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማስልጠኛ ማዕከል ለአስተዳደር ሰራተኞች በዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ቀን፡-ታህሳስ 02/2013 ዓ.ም
ቦታ፡- (ጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል)
አሰላ ከተማ (ETH-NADO ሀሙስ ታህሳስ 02/2013 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት 50 ለሚሆኑ ለጥሩነሽ ዲባባ ስፖርት ማሰልጠኛ ማዕከል አሰተዳደር ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እንዳሉት ስፖርተኞች ዶፒንግን በመተቀም ውጤታማና ሀብታም ብሎም ዝነኛ ለመሆን ከማሰብና ከግንዛቤ እጥረት በተያያዘ ችግሩ ከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ መምጣቱን አበራረትው፡፡ የስፖርቱ ወረርሽኝ የሆነውን ዶፒንግ ለመቆጣተርና ለመከላከል በየደረጃው የማሰልጠኛ ተቋማት አስተዳደር ሰራተኞች ለአትሌቶች ካላቸው ቅርበትና ኃላፊነት አንጻር አበክረው ሊሰሩ እደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻ ለተነሱት ጥያቆች እና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡
Image may contain: 1 person, sitting and indoor
Image may contain: one or more people, people sitting and indoor
Image may contain: one or more people, people sitting and indoor
Image may contain: 1 person

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *