ለአንደኛ ዙር የኢትዮጵያ ጠረፔዛ ቴኒስ የክለቦችና የተጋባዥ ክልሎች ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ አትሌቶች፤ ለቡድን አመራሮች፤ ለአሰልጣኞችና ለድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በዶፒንግና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ፡፡
ቦታ፤ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ አሰላ ከተማ
(ETH-NADO ህዳር 29/213 ዓ.ም) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ለአደኛ ዙር የኢትጵዮያ ጠረፔዛ ቴኒስ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ለሚሳተፉ አትሌቶች፤ለቡድን አመራሮች፤ ለአሰልጣኞችና ለድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግና ላይበአትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ማስልጠኛ አካዳሚ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመሰጠት ላይ ነው፡፡
በዚህ ሥልጠና ላይ ከ80 የሚበልጡ የክልቦችና የተጋባዥ ክልሎች አትሌቶች፤ አሰልጣኞች፤ የቡድን መሪዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ት ወ/ሮ ፋንታዪ ገዛኽ ኝ እንደተናገሩት ዶፒንግ የአገራችን ስፖርት ስጋት በመሆን ላይ መሆኑን ገልጸው ጽ/ቤታቸው በአገር አቀፍ ደረጃ የስፖርት አበረታች ቅመሞንችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስች የግንዛቤና የንቅናቄ መርኃግብሮችን ዘርግቶ ጠንክሮ እየሰራ መሆኑንም ም/ዋና ዳይሬክተሯዋ አብራርተዋል ፡፡
የሥልጠናው ዓላማ ለተተኪ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤያችውን ለማስጨበጥ የተዘጋጅ መድርክ ነው፡፡
በሥልጠናው ላይ በዶፒንግ ምንነት ፤በሚያስከትለው ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤ምርመራ ሂደትና በተዘረጉ ያሰራር ስርዓቶች በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች በሚል ርዕስ የተዘጋጁ ሰነዶች ቀርበዋል፡፡
በስልጠናው የዶፒንግ ታሪካዊ አመጣትና ምንንነት ፡ የአሰራር ስርዓቶች መተመለከተ የጽ/ቤቱ የትምህርት፤ስልጠናና የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ የተሰጠ ሲሆን፤ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ሂደት በተመለከተ በአቶ ዳንኤል ተስፋዩ የስልጠና ከፈተኛ ባለሞያ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ተስጥቷል፡
ሥልጠናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ ጠረፔዛ ቴኒስ ፌድሬሽን ጋር በትብበር የተዘጋጀ ነው፡፡